«የሀገራችን ኢኽዋኖች ተከታታይ ፅሁፍ»
√ #ክፍል 02
|• «የሱና ዑለማኦች ስለ ኢኽዋን ምን አሉ?»
በክፍል አንድ ባሰማሁት የድምፅ ፋይል ሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን «"ኢኽዋን ከአህለሱና ውጭ ነው የሚለው" ትክክል አይደለም። ያው አህለሱና የሆኑት ሊቃውንቶች ከአህለሱና ውጭ እንዳልሆነ አረጋግጠውለታል።» ማለታቸው ይታወሳል። እናም ዛሬ በአላህ ፍቃድ የሱና ዑለማኦች ስለ ኢኽዋን ምን እንዳሉ እንመልከታለን። ከዚያም ሸይኹ የተናገሩት እውነት ነው ወይስ በሱና ዑለማኦች ላይ፣ ወይ እየዋሹባቸው ወይ ያለ ዕውቀት አየመሰከሩባቸው የሚለውን እናረጋግጣለን።
√| ከዚህ በታች በአላህ ፍቃድና እገዛ ታላላቅ የሱና ዑለማኦች ስለ ኢኽዋን የተናገሩትን ለማቅረብ እሞክራለሁ።
1. ታላቁ ኢማም የዘመናችን ሙሐዲሥ ሸይኽ አል-አልባኒ (ረሒመሁላሁ) እንዲህ ይላሉ፦
|√ «ليس صوابا أن يقال إن الإخوان المسلمين هم من أهل السُنة لأنهم يحاربون السُنة» (من شريط فتوى حول جماعة التبليغ والإخوان من تسجيلات منهاج السنة في الرياض)
√| «አልኢኽዋን አል-ሙስሊሙን ከአህሉስ-ሱና ወል-ጀማዓ ናቸው ብሎ መናገር ትክክል አይደለም፤ ምክንያቱም እነርሱ ሱናን ይዋጋሉና።»
• ይህንን ሊንክ በመጫን ንግግራቸውን ማድመጥ ይቻላል። 14 years ago የተለጠፈ
https://youtu.be/d20Zb6JpAAA?si=KcLPeC_Zn2AQ-Sf0√|| «لا يجوز أن نقول "الخلاف بيننا وبين الإخوان المسلمين فرعي والإخوان المسلمون من أهل السنة" لا!. هم يحاربون أهل السنة ويقولون دعوتكم الآن تفرق. نحن عاشرناهم في سوريا وهنا.» (من أشرطة سلسلة الهدى والنور، الشريط رقم 356.)
√|| «"በእኛና በኢኽዋን አልሙስሊሚን መካከል ያለው ልዩነት በፈርዕ (በቅርንጫፍ ጉዳዮች) ላይ ብቻ ነው፣ ኢኽዋን ሙስሊሚንም ከአህሉስ-ሱና ናቸው።" ብሎ መናገር አይፈቀድም። በጭራሽ! (እንዴውም) እነሱ አህለሰሱናን ይቃወማሉ፤ (እኛንም) "ጥሪያችሁ አሁን ሰዎችን ትከፋፍላለች"ም እያሉ ነው። እኛ በሶሪያም እዚህም ከእነርሱ ጋር አብረን ኖረናል።»
• ይህንን ሊንክ በመጫን ንግግራቸውን ማድመጥ ይቻላል። 7 years ago የተለጠፈ
https://youtu.be/JDLVfowcQBk?si=-fxNGSlEv0IYvvu6√ ማሳሰቢያ፦
እንደሚታወቀው ኢኽዋን መልከ ብዙና በሸይኹ የህይወት ዘመን የተስፋፋ አንጃ በመሆኑ ሸይኹል አልባኒ ከህይወታቸው መጀመሪያ እስከ ህይወታቸው ፍጻሜ በኢኽዋኖች ላይ ተመሳሳይና አንድ አቋም አልነበራቸውም። ከእርሳቸው የፈትዋ የድምፅ ቅጅዎች እንደምንረዳውና ታሪካቸውን በቅርበት የሚያቁት ዑለማኦች እንደገለፁት ሸይኹ በአንጃው ሦስት መርሐላዎች (ደረጃዎች) ነበራቸው።
1• በመጀመሪያ ደረጃ ሸይኽ አል-አልባኒ ለኢኽዋን አልሙስሊሚን መልካም ግምት ነበራቸው። ምክንያቱም እነዚህ ኢኽዋኖች ቁርአንና ሱናን መከተልን መፈክራቸው ያደርጉ ነበርና። በዚህም የተነሳ እነርሱን ከሱና ውስጥ እንዳሉ ይቆጥሯቸው ነበር። ነገር ግን የዛኔም ቢሆን ከሱና ባያስወጧቸውም ከእነርሱ ይመለከቱ የነበረውን የዓቂዳ ድክመትና ወደተውሒድ ከመጣራት በላይ ለፖለቲካ የሚሰጡትን ትኩረት ይተቹ ነበር።
2• በሁለተኛው ደረጃ ሸይኽ አል-አልባኒ የኢኽዋን መንጋ ፈር መልቀቅ ግልጽ ይሆንላቸው ጀመር። ከዚያም አንዱ ኢኸዋኒይ የሰለፊያን ደዕዋ መተቸት ሲጀምርና “ሰለፊዮች የሚጨነቁት በውጫዊ ጉዳዮች ብቻ ነው” ብሎ የፃፈው ሲደርሳቸው የሸይኹ ትችት የበለጠ ጠነከረ። እንዲህም አሉ፦
«ما أعتقد أن سلفيًا عقيدةً وسلوكًا بإمكانه أن يتبنى منهج الإخوان المسلمين وأمثالهم»
ትርጉሙም፦ “በዓቂዳውም ሆነ በአካሄዱ ሰለፊይ የሆነ ሰው የኢኽዋን ሙስሊሚንንና እንደነሱ ያሉትን መንገድ ሊይዝ ይችላል ብዬ አላምንም።”
እናም ሸይኹ የኢኽዋን መንገድ ሰዎች የተለያዩ ዓቂዳዎች ቢኖራቸውም ሁሉንም በአንድ የፖለቲካ ቡድን ውስጥ ለመሰብሰብና ለማደራጀት የሚሞክር መንገድ መሆኑ ግልጽ እየሆነላቸው መጣ። ሆኖም ግን ሸይኹ ኢኽዋንን ከሌሎች ቡድኖች ይልቅ ወደ ሐቅ የቀረቡ እንደሆኑ ይናገሩ ነበር፦
«الإخوان المسلمون هم أقرب الجماعات إلى الحق، لكنهم ليسوا على الحق.»
ትርጉሙም፦ “ኢኽዋን አልሙስሊሚን ከቡድኖች ሁሉ ወደ እውነት የቀረቡ ናቸው፤ ነገር ግን እነርሱ በእውነት ላይ አይደሉም።”
3• በመጨረሻው ደረጃ ሸይኽ አል-አልባኒ የኢኽዋን ሙስሊሚንን አቋም በግልጽ መቃወም ጀመሩ። እነርሱ ከሚያስተካክሉት ይልቅ የሚያበላሹት እንደሚበዛ እና ብዙ መሰረታዊ ስህተቶችን ሲመለከቱ እንዲህ ሲሉ የመጨረሻ አቋማቸውን አወጁ፦
«خلافنا مع الإخوان المسلمين خلافٌ في الأصول لا في الفروع فقط.»
“ከኢኽዋን አልሙስሊሚን ጋር ያለን ልዩነት በመሠረታዊ ጉዳዮች ነው፤ በቅርንጫፍ ጉዳዮች ብቻ አይደለም።”
እንዲሁም ከላይ እንዳሰፈርኩት፦
«ليس صوابًا أن يقال الإخوان المسلمون من أهل السنة، لأنهم يحاربون السنة.»
“ኢኽዋን አልሙስሊሚን ከአህሉስ-ሱና ናቸው ማለት ትክክል አይደለም፤ ምክንያቱም ሱናን ይዋጋሉና።” ሲሉ ኢኽዋን ከአህለሱና አመሆናቸውን አረጋግጠዋል።
እናም ሸይኹ መጀመሪያ ላይ እነርሱ ቁርአንና ሱናን እንከተላለን ብለው በሚያሳዩት መፈክር ላይ የተመሠረተ መልካም ግምት ነበራቸው። በኋላ ግን የቡድኑ እውነተኛ መንገድና ተግባራዊ ጥመታቸው ሲገለጥላቸው አቋማቸውን እንደቀየሩ ነው ታሪክ የሚነግረን።
ስለዚህ የዑለማዎችን ንግግር በታሪካዊና በጊዜያዊ አውዱ መሠረት መረዳት የፍትሕ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የዕውቀታዊ ታማኝነትም ጉዳይ ነው። አንድን የዓሊም ንግግር ከተናገረበት ደረጃና አውድ ነጥሎ ለሌላ ዓላማ መጠቀም ትክክል አይደለም።
በዚህ ረገድ ሸይኽ አሕመድ ሙሐመድ አስሷዲቁ አንነጃር በ blogpot ገፃቸው
«موقف الشيخ الألباني من جماعة الإخوان المسلمين»
በሚል ርዕስ የለጠፉትን ያንብቡ፦
http://abuasmaa12.blogspot.com/2025/10/blog-post_20.htmlየሌሎች ዑለማኦችን ንግግር በቀጣይ ክፍል አቀርባለሁ ኢንሻአላህ።
√ #ክፍል 01
=
(አቡ ዒምራን፣ ነሃሴ 11/2018)
የቴሌግራም ቻናል