🔥 አሸባሪዎችና ንጉሡ በመስጂድ አል-ሐራም ፦
... و ما الاعتداء الارهابي الظلوم على الملك عبد العزيز بن عبد الرحمن الفيصل ال سعود طيب الله ثراه الا صورة من صور الارهاب الظالمة المظلمة ذلك أنه كان يطوف بالبيت صباح يوم الجمعة سنة 1353ه طواف الافاضة فبينما هو في الشوط الرابع من طوافه و معه ابنه الأكبر سعود بن عبد العزيز
و معهما ثلة قليلة من رجال الامن و الحراس فاذا برجل غادر فاجر يخرج من الفجوة الشامية من حجر اسماعيل و قد استل خنجرا و صاح صيحات منكرة و اندفع نحو الملك فتصدى له الشرطي أحمد بن موسى العسيري الا أن الغادر عاجله فطعنه فقتله ثم تصدى للغادر الملحد جندي اخر فقتله و تصدى
له أحد رجال الحرس الملكي فأطلق عليه رصاصة فأرداه قتيلا ثم خرج مجرم ثاني فتصدى له جندي من الحرس فقتله فخرج ثالث فرأى ذعرا فولى هاربا و أدركته رصاصة أحد رجال الأمن فخر صريعا و أمر الملك بقفل الأبواب حتى أكمل طوافه و حرصوا على كتم ما حصل لئلا يلحق الحجاج شيء من الخوف
و القلق فيؤثر في حجهم و كان الارهابيون ثلاثة ممن امتلأت قلوبهم غلا و حقدا و حسدا لهذا الامام الذي أحيا الله بامامته السنن فارتفع علمها مرفوفا على الجزيرة و انتشرت دعوة الهدى و النور حتى بلغت الافاق البعيدة في أرض الله المديدة شرقا و غربا و شمالا و جنوبا فرحمه الله و طيب ثراه و جعل الجنة مأواه و النار لأعداء دين الله الذين يحرصون دائما على نشر الفساد في أرض الله.
من كتاب الارهاب و اثاره على الأفراد و الأمم
للشيخ زيد بن محمد بن هادي المدخلي
... ግፈኛ ሽብርተኞች በንጉሥ ዐብዱልአዚዝ ቢን ዐብዱረሕማን አል-ፈይሰል አሊ-ሰዑድ ላይ የፈጸሙት አሰቃቂ የሽብር ጥቃት ነው። -አላህ ቀብሩን መልካም ያድርግለት- (ይህ ግፍ) የበዳይና የመበደል ሽብርተኝነት አንድ ምሳሌ ነው።
ይህም የሆነው (ንጉሡ) በ1353 ዓ.ሂ (1934 ዓ.) "ጁምዓ" ጠዋት “ ጠዋፍ አል-ኢፋዳን ” (በካዕባ ዙሪያ) ሲያደርግ ነበር። በአራተኛው ዙር ላይ እያለ ከበኩር ልጁ ሳዑድ ቢን ዐብዱልዓዚዝ ፣ ከጥቂት የደህንነት ሰራተኞች እና ጠባቂዎች ጋር በመሆን አብረውት ነበሩ።
በዚህ ሁኔታ እያሉ አንድ ተንኮለኛ እና ክፉ ሰው ከ "ሀጅር ኢስማኤል" (የኢስማኤል ድንጋይ) አጠገብ (ከካዕባ አጠገብ ካለው ከፊል ክብ ግድግዳ) ከሻሚያ ክፍተት ወጣ። ጩቤ በመምዘዝ በጸያፍ መፈክሮች ጮኸና ወደ ንጉሱ ሮጠ።
የፖሊስ አዛዥ የነበረው አሕመድ ቢን ሙሳ አል-ዐሲሪ ገጠመው ፤ ነገር ግን ተንኮለኛው ሰው በመጀመሪያ አጠቃውና ወግቶ ገደለው። ከዚያም ሌላ ወታደር ገጠመው አምላክ የለሹ "ሙልሒድ" ገደለው። ከዚያም የንጉሣዊው ጥበቃ አባል የሆነ ወታደር ተኩሶ ገደለው።
ከዚያም ሌላ ሁለተኛ አመፀኛ "ሙጅሪም" ወጣ ። ነገር ግን አንድ ጠባቂ ገጠመው እና ገደለው። ሌላ ሶስተኛም ሰው ብቅ አለና በድንጋጤ አይቶ ሸሸ ! ነገር ግን ከደህንነት ሰራተኞች በአንዱ ጥይት ተመቶ ሞተ።
ንጉሡ ጠዋፍ እስኪጨርስ ድረስ በሮቹ እንዲዘጉ አዘዘ !
ምዕመናኑ በሐጅ ስነ-ስራታቸው ላይ ተጽዕኖ እንዳያሳድርባቸው እንዲሁም ፍርሃትና ጭንቀት ውስጥ በመግባት እንዳይጨናነቁ በሚል ክስተቱ በሚስጥር ለመጠበቅም ጥረት በማድረግ ተጠነቀቁ !
አሸባሪዎቹ ልባቸው በዚህ ኢማም ላይ በክፋት ፣ በጥላቻና በቅናት የተሞላ ሦስት ሰዎች ነበሩ !
አላህ ሱናን በዚህ ኢማም አመራር አማካኝነት አነቃቃው ! ሰንደቁም በባሕረ ሰላጤው ሀገራት ላይ ከፍ ብሎ ከፍ ከፍ አለ ! የምራቻና የብርሃን ጥሪ በሰፊው ምድር ላይ ምስራቅና ምዕራብ ፣ ሰሜንና ደቡብ ፣ እሩቅ አድማስ እስኪደርስ ድረስ ተሰራጨ።
አላህ ይዘንለት !!! መቃብሩን መዓዛ ያድርግለት ፣ ጀነትንም መኖሪያው ያድርግለት ! የጀሀነም እሳት ለአላህ ዲን ጠላት ለሆኑትና ምድር ላይ ብልሽት ለማስፋፋት ሁልጊዜ ለሚተጉ ለሆኑት የኢስላም ጠላቶች ያድርገው !!!
ምንጭ ፦ (አል-ኢርሃብ ወአሳሩኡ ዐለል አፍራድ ወል-ኡመም)
(( ታላቁ ሼይኽ ዘይድ ቢን መሐመድ ቢን ሀዲ አል-መድኸሊ ))
https://t.me/amr_nahy1📝 … ኢስማኤል ወርቁ...